Share

አሴክሿሊቲ ምን ማለት ነው?

አሴክሿል የሆነ ሰው እምብዛም የወሲብ ፍላጎት ያለው ወይም ከነጭራሹ ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት የሌለው ሰው ነው።

የወሲብ መስህብ፣ በመሠረታዊ አገላለጽ፣ ለአንድ ሰው ወሲባዊ ተማርኮ ሲኖርህ እና ከእነሱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ስትፈልግ ነው።

አሴክሿል ሰዎች፣ የወሲብ ፍላጎት የላቸውም ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀም አይፈልጉም። ይህ ሲባል ግን አሴክሿል መሆን ማለት ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም ሊኖረው ይችላል። አንዳንድ ሰዎች የወሲብ መስህብ የሚኖራቸው በተወሰኑ ነገሮች ብቻ ይሆናል። ለምሳሌ ያህል ዴሚሴክሿል የሆነ ሰው፤ አንዳንድ ጽሁፎችህ እንደሚገልጹት በ አሴክሿል ዣንጥላ ውስጥ ይካተታል። ዴሚሴክሿሎች የወሲብ መስህብ የሚኖራቸው ከአንድ ሰው ጋር በጣም ጥልቅ የሆነ ትውውቅን ሲያዳብሩ ነው። በሌላ አባባል ስናስቀምጠው የወሲብ ፍላጎት ወይም የወሲብ መስህብ የሚኖራቸው ጥልቅ የሆነ ፍቅር ለፍቅር  አጋራቸው ሲኖራቸው ነው። አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት ሳይኖራቸው የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ለማድረግ ሊመርጡ ይችላሉ። ይህ የሚያሳየው የተለያዩ ሰዎች የተለያየ አይነት አሴክሿል ሊሆኑ ይችላሉ ስለዚህ አሴክሿል መሆን አንድ መንገድ የለውም።

አንዳንድ ሰዎች የወሲብ መስህብ በጭራሽ የላቸውም

አሴክሿል ሆኖ ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት የሌለው ሰው ሌላ አይነት መስህብ ለሰው ሊኖረው ይችላል። ከወሲብ መስህብ ውጪ ከታችህ የተዘረዘሩት መስህቦች ሊኖሩት ይችላሉ፤

  • የፍቅር መስህብ ፡ ከአንድ ሰው ጋር ጥልቅ የሆነ የፍቅር ግንኙነትን መፈለግ።
  • የውበት መስህብ ፡ በሰው መልክ መማረክ ወይም መሳብ።
  • አካላዊ መስህብ፡ አንድን ሰው መንካት፣ መያዝ ወይም ማቀፍ መፈለግ።
  • የጓደኝነት መስህብ፡ ከአንድ ሰው ጋር ጓደኛ ለመሆን መፈለግ።
  • ስሜታዊ መስህብ: ከአንድ ሰው ጋር ስሜታዊ ግንኙነት መፈለግ።

አሴክሿል ሰዎች እነዚህ የመስህብ ዓይነቶች እና ሌሎች ብዙ ሊኖራቸው ይችላሉ። አሴክሿል ሰዎች የወሲብ ፍላጎት ሊኖራቸው እና ሊሰማቸው ይችላል።

አሴክሿል ሰው በብዙ ምክንያቶች ግብረስጋ ግንኙነት ሊፈጽም ይችላል፡ ከእነዚህም መካከል፡-

  • የወሲብ ፍላጎታቸውን ለማርካት
  • ልጅ ለመውለድ
  • የፍቅር አጋራቸውን ለማስደሰት
  • በወሲብ የሚገኘውን አካላዊ ደስታ ለማግኘት
  • ፍቅርን ለማሳየት እና ለመቀበል
  • በመንካት እና በመተቃቀፍ የሚገኘውን ወሲባዊ ደስታ ለማግኘት

እርግጥ ነው፣ አንዳንድ አሴክሿል ሰዎች ምንም ዓይነት የወሲብ ፍላጎት የላቸውም – እና ያ ደግሞ ምንም ማለት አይደለም ምክንያቱም አሴክሿልነት ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም ስላለው።

አሴክሿል መሆኔን እንዴት ማወቅ እችላለው?

ምንም እንኳን አሴክሿል መሆን አለመሆንዎን ለማወቅ የተለየ ፈተና መውሰድ ባይችሉም, ፍላጎቶችዎን ለመገምገም እና ከተለመዱት የአሴክሿል ባህሪያት ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት እራስዎን ጥቂት ቁልፍ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላሉ።

  • ወሲባዊ መስህብ ለእኔ ምን ማለት ነው?
  • ወሲባዊ መስህብ ለሌላ ሰው አለኝ?
  • ስለ ወሲብ ምን አይነት አመለካከት አለኝ?
  • ሌሎች ስለሚጠብቁት ብቻ ለወሲብ ፍላጎት እንዲኖረኝ ሆኖ ይሰማኛል?
  • ወሲብ ለእኔ አስፈላጊ ነው?
  • ማራኪ ሰዎችን አይቼ ከእነሱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የመፈጸም ፍላጎት ይሰማኛል?
  • ፍቅር ማሳየት የምወደው እንዴት ነው? በወሲባዊ ግንኙነት ነው?

እነዚህ ጥያቄዎች ምንም እንኳን “ትክክል” ወይም “የተሳሳቱ” መልሶች ናይኖራቸውም  ስለ ፍላጎትዎ እንዲያስቡ ሊረዱዎት ይችላሉ።

Share

Discover more from Addis Alliance

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading