Share

የዘር ፈሳሽን አለመቆጣጠር

ቶሎ ብትጨርስ ችግር አለው?

ከሚፈለገው በላይ ቶሎ ቶሎ መጨረስ በጣም የተለመደ ነው – ከብዙ ወንዶች ግማሽ ያህሉ ከሚፈልጉት በላይ በፍጥነት የሚጨርሱበት ጊዜ እንደ ነበረ ይናገራሉ። ምንም የሚያስጨንቅ ነገር አይደለም፣ እና እንደ መደበኛ የሚቆጠርባቸው አንዳንድ ሁኔታዎችም አሉ ለምሳሌ፡-

  • በጣም አስደሳች እና አነቃቂ ሁኔታዎች፣ ወይም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከፈጸሙ ወይም ማስተርቤት ካደረጉ ብዙ ጊዜ ሲቆጠር
  • ወንዶች ወጣት ሲሆኑ – በ 20 ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ወንድ ወደ ግንኙነት በመፈጸም እና የዘር ፈሳሽ በማፍሰስ መካከል ያለው አማካይ ጊዜ ከ 3 ደቂቃ ያነሰ ነው።
  • አንድ ወንድ ሲደክመው ወይም ሲጨናነቅ።

ነገር ግን፣ በየጊዜው የሚከሰት ከሆነ፣ ለእርስዎ እና ለወሲብ አጋርዎ የሚያበሳጭ እና የማያረካ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም በግንኙነታችሁ ውስጥ ውጥረትን ሊያስከትል ይችላል። ይህ ችግር አሳሳቢ ከሆነ በቁም ነገር መውሰድ እና አንድ ነገር ማድረግ ጠቃሚ ነው።

ሰዎች ለምን በፍጥነት ይጨርሳሉ?

አልፎ አልፎ አካላዊ ምክንያቶች አሉ፤ ለምሳሌ እንደ ፕሮስታታይተስ (prostatitis) ያሉ የሕክምና ሁኔታዎች።። ነገር ግን ከሚከተሉት በአንዱ ምክንያት የመከሰቱ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

  • ስለ ግንኙነቱ መጨነቅ፣ በተለይም ከአዲስ የወሲብ አጋር ጋር። አንዱ ወይም ሁለታችሁም ልምድ ከሌላችሁ (ይህ አንዳንድ ጊዜ የወሲብ ግንኙነት ጭንቀት ይባላል)።
  • በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖችን (ኤችአይቪን ጨምሮ) ስለመያዝ ወይም ስለማስተላለፍ መጨነቅ
  • የጥፋተኝነት ስሜት (አብዛኛው ሰው ወሲብ ሃጢያተኛ፣ ቆሻሻ ወይም አሳፋሪ ነው ብለው በማመን ያደጉ ናቸው)።
  • የግብረ ስጋ ግንኙነቱ በፍጥነት ማለቅ ካለበት ወይም በሚስጥር ከሆነ።
  • የፍቅር ግንኙነት ጉዳዮች፣ ለምሳሌ ያልተፈቱ ክርክሮች ካሉ፣ ወይም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም ግፊት ሲኖር;
  • በፍቅረኞች መካከል ያለው ልዩነት ወይም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለበት አስተሳሰብ ላይ ልዩነት እና፤
  • ሌሎች ጭንቀቶች ለምሳሌ ስለ ሥራ ወይም ገንዘብ።

በእውነቱ የማይረዳው ምንድን ነው?

  • በወሲብ ወቅት ትኩረትን የሚከፋፍሉ ወይም የማያነቃቁ ሀሳቦችን ማሰብ;
  • የህመም ማስታገሻ ማደንዘዣ ክሬም መጠቀም;
  • በቅድመ-ጨዋታ ላይ ትንሽ ጊዜ ማሳለፍ ወይም ችላ ማለት
  • ስሜታዊነትን ለመቀነስ ሁለት ኮንዶም መጠቀም፣ ይህ ኮንዶሙን እንዲቀደድ የማድረግ ዕድሉን ከፍተኛ ያደርገዋል።
  • አልኮል መጠጣት እና
  • ቪያግራ ወይም ተመሳሳይ መድኃኒቶችን መጠቀም።

ምንም እንኳን እነዚህ ሁሉ ነገሮች የዘር ፈሳሽ መርጨትን ለማዘግየት ሊረዱህ ቢችሉም በምትጨርስበት ጊዜ የበለጠ በራስህ እንድትቆጣጠር አይረዱህም እና ወሲብን ብዙም አስደሳች አያረጉትም። የዚህ ጽሑፍ አላማው ወሲብን የበለጠ እንዲደሰቱበት ለማድረግ እና የወሲብ ኦርጋዝዎም መቆጣጠር እንዲማርበት መርዳት ነው።

ምን ይረዳል?

  • በወንድ ብልትህ ላይ ምንም ችግር እንደሌለው ማስታወስ፣
  • በወሲብ ጊዜ ስሜታችሁ ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግ። ስለ አጨራረስ ከማሰብ ይልቅ በመስጠት እና በመቀበል ላይ ባለው ሰአት እኩል መደሰት በጣም አስፈላጊ ነው።

በምትጨርስበት ጊዜ በተሻለ ሁኔታ መቆጣጠር እንድትችል ለመማር የሚረዱህ ልምምዶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱን እያቸው።

1. የማቆም-መጀመር ቴክኒክ

ይህንን ቴክኒክ ብቻህን ወይም ከወሲብ አጋርህ ጋር ማድረግ ትችላለህ። በጣም ቀላል ነው።

ብልትህን በሚመችህ መንገድ አነቃቃው ወይም የወሲብ አጋርህ እንዲረዳህ አድርግ። በብልትህ እና በተቀረው የሰውነትህ አካል ላይ ባሉ ስሜቶች ላይ አተኩር። ስሜትህ በጣም ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ ( ለመጨረስ ስቃረብ) እራስህን ማነቃቃት አቁም።

ለ 20 – 30 ሰከንዶች እረፍት ማድረግ ፣ ወይም የመጨረስ ስሜትህ እስኪቀንስ ድረስ። ብልትህ ሊሞትብህ ይችላል ይህ ምንም ማለት አይደለም። ከዚያም ማነቃቂያውን እንደገና ጀምር እና እንደበፊቱ ቀጥል። ቴክኒኩን አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ድገመው። ለመጨረሻ ጊዜ ስታደርገው እስክትጨርስ ድረስ ማነቃቂያውን መቀጠል ትችላለህ።

ብልትህ መልሶ መቆም ካልቻለ አትጨነቅ። ብቻህን ከሆንክ በቀላሉ ወደ ቴክኒኩ ሌላ ጊዜ መመለስ ትችላለህ፣ ከወሲብ አጋርህ ጋር ከሆንክ በምትኩ እሱን ማነቃቃት ትችላለህ ወይም ለሌላ ጊዜ መተው ትችላለህ።

ይህን ቴክኒክ መለማመዱ ልክ የዘር ፈሳሽ ከመምጣቱ በፊት የሚሰማህን ስሜት እንድታውቀው እና ስሜትህን እንዴት ቀንሰህ ለብዙ ሰአት መቆየት እንደምትችል ለማወቅ ይረዳሃል። ይህንን ልምምድ በሳምንት ውስጥ ብዙ ጊዜ መለማመድ ትችላለህ በመጨረሻም መጨረስ የምትፈልግበትን ሰአት አንተ መቆጣጠር እንደምትችል ትረዳለህ። ይህን ቴክኒክ ተጠቅመህ እራስህን ማቆየት ከቻልክና የበለጠ በራስ መተማመን ካገኘህ በኋላ ከወሲብ አጋርህ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ስትፈጽም ተመሳሳይ ዘዴዎችን መጠቀም ትችላለህ።

2. የመጭመቅ ቴክኒክ

የወሲብ አጋር ካለህ የማቆም-መጀመር ቴክኒክ ላይ የመጭመቅ ቴክኒክን ጨምሮ መጠቀም ይቻላል።

እንደበፊቱ ሁሉ የወሲብ አጋርህ የዘር ፈሳሽ ለማፍሰስ እስክትጠጋ ድረስ ብልትህን ያነቃቃልህ። ለመጨረስ ስትቃረብ ብልትህን ከጭንቅላቱ ስር ጭምቅ አድርጎ ይያዘው ይህም ሊመጣ ያለውን ስሜት ይቀንሳል፣ እና ሳትረጭ እንድትቆይ ያደርጋል። ይህን ቴክኒክ እንደ ማቆም-መጀመር ቴክኒክ በተደጋጋሚ መቀጠል ይቻላል።

ይህን ቴክኒን ወሲብን ለማራዘም መጠቀም ትችላለህ። መሻሻልህን ከማየትህ በፊት እነዚህን ዘዴዎች ለጥቂት ጊዜ መለማመድ ያስፈልግህ ይሆናል። ይሁን እንጂ እነሱን ለመማር ትንሽ ጊዜ መውሰድ ጠቃሚ ነው፤ ምክንያቱም ለእርስዎ እና ለባልደረባዎ የወሲብ ደስታን ያራዝማል፤ ያጠናክራል። በወሲብ ጊዜ ረዘም ላለ ጊዜ ለመቆየት ልምምድ ከተለማመድህ ቀላል ይሆናል።

Share

Discover more from Addis Alliance

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading