የግንኙነት አይነቶች እና የኤችአይቪ ቫይረስ ተጋላጭነታቸው
መሳሳም
መሳሳም የኤች አይቪ ቫይረስን የማያስተላልፍ ሲሆነ ነገር ግን በከንፈር እና በአፍ ውስጥ ቁስል ካለ፤ የከንፈር መሰንጠቅ እና የከንፈር እና የድድ መድማት ካለብን ግን የመተላለፍ እንዱል ይጨምራል፡፡
አንድ ላይ ግለ ወሲብ (ሴጋ) ማድረግ
የኤችአይቪ ቫይረስ ሰውነትን በመተሻሸት እና አንድ ላይ ግለ ወሲብ (ሴጋ) በማድረግ አይተላለፍም ነገር ግን የሌላውን ሰው የዘር ፈሳሽ እንደ ማለስለሻ በመጠቀም የሚደረግ ግለ ወሲብ የዘር ፈሳሹ በሽንት ቧንቧችን በኩል እንዲገባ እድል ስለሚሰጥ ለኤችአይቪ ቫይረስ ተጋላጭ ልንሆን እንችላለን፡፡
በአፍ የሚደረግ ግንኙነት
በአፍ በሚደረግ ግንኙነት ወቅት የኤች አይቪ ቫይረስ የሚተላልፍበት መንገድ በከንፈራችን፣ ድድ እና አፍ ውስጥ ቁስለት ወይም መድማት ካለ ተጋላጭነታችን ይጨምራል ይህም ቫይረሱ በቀላሉ ከብልት ወደ የደም ዝውውር ስርአታችን ቀላል መግቢያ መንገድ ይፈጥርለታል::
በአፍ የሚደረግ ግንኙነት የኤች አይቪ ቫይረስ ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች ያጋልጠናል፡፡
በአፍ እና በፊንጢጣ የሚደረግ ግንኙነት
በአፍ እና በፊንጢጣ የሚደረግ ግንኙነት በአብዛኛው ለኤችአይቪ ቫይረስ ባያጋልጠንም ለሌሎች ለተለያዩ እንደ ሄፒታይተስ የጉበት ቫይረስ ላሉ የአባላዘር በሽታዎች ያጋልጠናል፡፡
ከታ (ቦተም) ሆኖ በፊንጢጣ የሚደረግ ግንኙነት
ከሁሉም የግንኙነት አይነቶች ውስጥ ከታ (ቦተም) ሆኖ በፊንጢጣ የሚደረግ ግንኙነት ለኤችአይቪ ቫይረስ ተጋላጭነት ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል፡፡ ኤች አይቪ ቫይረስ ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ የአባላዘር በሽታዎችም ተጋላጭነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ በተፈጥሮ የፊንጢጣ ግድግዳ ከሰውነታችን ሁሉ ስስ በመሆኑ የኤችአይቪ ቫይረስ በቀላሉ ወደ የደም ዝውውራችን እንዲገባ ይረዳዋል፡፡
ሁልጊዜ ኮንዶም እና ውሃ ነክ ማለስለሻዎችን አብሮ መጠቀም ይመከራል፡፡
ከላ (ቶፕ) ሆኖ በፊንጢጣ የሚደረግ ግንኙነት
ከላ ሆኖ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ለኤች አይቪ ቫይረስ ያለንን ተጋላጭነት ይጨምራል፡፡ በተለምዶ ከላ መሆን ተጋላጭነት የለውም የሚለው አስተሳሰብ ፈጽሞ የተሳሳተ እና መታረም ያለበት ነው፡፡ ሁልጊዜ ኮንዶም እና ውሃ ነክ ማለስለሻ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
በሴት ብልት የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት
በሴት ብልት የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አንደኛው የኤች አይቪ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታዎች መተላለፊያ ስለሆነ በየትኛውም ጊዜ ኮንዶምን መጠቀም ይመከራል፡፡
በአፍ እና በሴት ብልት ለሚደረግ ግንኙነት ደግሞ ዴንታል ዳም በማድረግ መከላከል ይቻላል፡፡

