የማሕፀን በር ካንሰር
የማሕፀን በር ካንሰር ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በብዛት እድሜያቸው ከ ሠላሳ አምስት ዓመት በታች በሆኑ ሴቶች ላይ የሚገኝ የካንሰር አይነት ነው፡፡
የማሕፀን በር ካንሰር በምን ይመጣል ?
የማሕፀን በር ካንሰር የሚመጣው በማሕፀን በር አካባቢ የሚገኙ ሕዋሶች የልተለመደ ለውጥ ሲያመጡ የሚከሰት ነው፡፡ እነዚህ ለውጦች እንዲመጡ የሚያደርጉ ትክክለኛ ምክንያቶች እስካሁን ምን እንደሆኑ ባይረጋገጡም ነገር ግን ለእነዚህ ለውጦች ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጋሉ ከሚባሉት ምክንያቶች መካከል የሚከተሉት ናቸው፡፡
- የሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሽን
- የደከመ የበሽታ የመከላከል አቋም እና
- ሲጋራ ማጨስ ናቸው
ሲጋራ አለማጨስ እና ጥንቃቄ የተሞላው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡
የማሕፀን በር በሽታ ምልክቶች ምንድናቸው ?
ሕመሙ የመጀመርያ ደረጃ ላይ ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል ነገር ግን ምልክት ማሳየት ሲጀምር ቀጥሎ የተዘረዘሩት ምልክቶች ይታያሉ
- ከግንኙነት በኋላ የብልት መድማት፡፡
- ከወር አበባ ወቅት ውጪ ደም መታየት፡፡
- በግንኙነት ወቅት የሕመም ስሜት፡፡
- ያልተለመደ የብልት ፈሳሽ እና
- የወር አበባ ማየት ባቆሙ ሴቶች ላይ ደም መታየት ናቸው፡፡
ሕክምናው ምንድነው ?
ሕክምናው እንደየ ማሕፀን በር ካንሰር ደረጃው የሚለያይ ሲሆን የመድኀኒት ሕክምና፣ የራዲዮቴራፒ እና የቀዶ ጥገና ሕክምና በተናጠል ወይም በአንድነት ሊሰጥ ይችላል፡፡
ማንኛዋም ሴት በየሦስት ዓመት የማሕፀን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ እንድታደርግ ይመከራል፡፡

