Share

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የምንለው ሕመም ፊኛን፣ኩላሊትን እና ተያያዥ የሽንት ቧንቧዎችን  የሚያጠቃ  በሽታ ነው፡፡የሽንት ቧንቧ  ኢንፌክሽን ማንኛውንም ሰው የሚያጠቃ ሲሆን በአብዛኛው ግን በሴቶች ላይ  ይከሰታል ይህም አጭር የሽንት ቧንባ  ሰላላችው  እና ለፊንጢጣቸው ቅርብ ሰለሆነ ነው፡፡

የሽንት ቧንቧ  ኢንፌክሽን ምልክቶች

የታችኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን  ፊኛ  እና ዩሬትራ ኢንፌክሽን ምልክቶች

  • ቶሎ ቶሎ  ሽንት የመምጣት ሰሜት፡፡
  • በምንሸናበት ጊዜ ሕመም ወይምተ ያለመመቸት ሰሜት መሰማት፡፡
  • ለመሽናት ማጣደፍ፡፡
  • ሽንትን ሙሉ ለሙሉ ያለመሽናት ስሜት፡፡
  • የታችኛው የሆድ እቃ ክፍል ሕመም፡፡
  • የደፈረሰ፣ደም ያለው ወይም የሚሸት ሽንት መሽናት፡፡
  • በአጠቃላይ የድካም እና የሕመም  ስሜት መሰማት ናቸው፡፡

የላይኛው የሽንት  ቧንቧ ኢንፌክሽን ኩላሊት  እና ዩሬተር (ኩላሊትን ከ ፊኛ ጋር የሚያገናኘው  ትቦ) ምልክቶች

  • ትኩሳት ከ38 ዲግሪ ሴንትግሬድ በላይ መሆን፡፡
  • የጎን ሕመም ወይም ውጋት መሰማት፡፡
  • ብርድ ብርድ ማለት እና ማንቀጥቀጥ፡፡
  • እረፍት ማጣት፡፡
  • ባጠቃላይ የሰውነት ሕመም መሰማት እና ድካም፡፡

የታችኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ከላይኛው በአብዛኛው ቢከሰትም ከፍተኛ ጉዳት አያመጣም በተቃራኒው ግን የላይኛው የሽንት ቧንቧ  ኢንፌክሽን ግን የኩላሊት ጉዳት እና የደም ዝውውር መበከልን ያስከትላል፡፡

ወደ ሕክምና መቼ መሄድ አለብን ?
  • የላይኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን  ምልክት ሲኖረን፡፡
  • የታችኛው የሽንት ቧንቧ ምልክቶቹ እየባሰ ከሄደ እና ምንም ለለውጥ ከሌለው፡፡
  • ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶ ች የሚታዩብን ከሆነ፡፡
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን  ሕክምና

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን በአብዛኛው ለአጭር ጊዜ በሚወሰዱ መድኀኒቶች ይድናል፡፡ ለወንዶች እና ለነፍሰ ጡር ሴቶች የሕክምና ጊዜው ሊረዝም ይችላል፡፡የበሽታው ምልክቶች በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊጠፉ ቢችልም መድኀኒቱን ጨርሰን መውሰድ አለብን፡፡ መድኀኒቱን ከጨረስን በኋላ  ያልተሻለን ወይም የባሰብን ከሆነ ተመልሰን ወደ ሐኪም ቤት መሄድ  አለብን፡፡

የሽንት  ቧንቧ  ኢንፌክሽን መምጫ  መንስኤዎች

የሽንት  ቧንቧ  ኢንፌክሽን በአብዛኛው  በባክቴርያ ምክያት የሚመጣ ሲሆን ለዚህም ታጋላጭነትን  የሚጨምሩ ምክንያቶችም ቀጥሎ  የተዘረዘሩት ናቸው፡፡

  • እንደ የኩላሊት ጠጠር ያሉ የሽንት ቧንቧን የሚዘጉ ነገሮች፡፡
  • ሽንትን በጊዜ እና ጨርሶ  አለመሽናት፡፡
  • የስኳር ሕመም ፡፡
  • በሽታን የመከላከል አቅምን የሚጎዱ እነደ ኤችአይቪ እና ኬሞ ቴራፒ፡፡
  • የተለቀ ፕሮስቴት ዕጢ በወንዶች ላይ፡፡
  • አርቴፍሻል የሽንት ማስወገጃ  ትቦ  ፡፡
የመከላከያ  መንገዶች
  • አዘውትሮ ፈሳሽ መውሰድ::
  • ሽንት በመጣ ሰአት በጊዜ መሽናት::
  • ከጥጥ የተሰሩ የውስጥ ሱሪዎችን መጠቀም::
  • የሚያጠብቁ ልብሶችን  አለማድረግ::
  • ለሴቶች ዐይነ ምድር ከተጸዳዱ በኋላ ከፊት ወደ ኋላ ማጽዳት::

 

 

Share

Discover more from Addis Alliance

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading