በአፍ የሚደረግ የተራክቦ ሥጋ ግንኙነት እና የኤችአይቪ ተጋላጭነት
በአፍ የሚደረግ የተራክቦ ሥጋ ግንኙነት ማለት በአፍ እና በምላስ የወንድ ብልትን፣ የሴት ብልትን እና ፊንጢጣን መላስ ወይም መጥባትን ያጠቃልላል ስለዚህም እነዚህ የግንኙነት አይነቶች ለኤችአይቪ ቫይረስ ያጋልጡናል፡፡
በአፍ የሚደረግ የተራክቦ ሥጋ ግንኙነት በሴት ብልት እና በፊንጢጣ ከሚደረግ የተራክቦ ሥጋ ግንኙነት ባነሰ መልኩ ለኤችአይቪ ቫይረስ የሚያጋልጥ ቢሆንም ይህ ግን ቫይረሱ ፈጽሞ አይተላለፍም ማለት አይደለም፡፡
ለኤችአይቪ ቫይረስ ተጋላጭነትን ከሚጨምሩ ምክንቶች መካከል የአፍ ውስጥ ቁስል፣ የሚደሙ ድዶቸ መኖር፣ የብልት ቁስል እና የሌሎች የአባላዘር በሽታዎች መኖር ይጠቀሳሉ፡፡ በአፍ የሚደረግ የተራክቦ ሥጋ ግንኙነት ለወሲብ ጓደኛችን ማድረግ ለእኛ ከሚደረግልን ግዜ በይበልጥ ተጋላጭነታችንን ይጨምራል በዚህም በአፍ የተራክቦ ሥጋ ግንኙነት ወሲብ ጓደኛችንን በምናደርግበት ወቅት የወንድ የዘር ፈሳሽን አፍ ውስጥ ማፍሰስ ከፍተኛ ተጋላጭነትን ያስከትላል፡፡
በአፍ ግንኙነት የሚደረግለት ሰው ኤችአይቪ ቫይረስ ካለበት ቫይረሱ በወንድ የዘር ፈሳሽ፣ በሴት ብልት ፈሳሽ እና በፊንጢጣ ፈሳሽ ውስጥ ስለሚገኝ በአፋችን በኩል ወደ ሰውነታችን ሊገባ ይችላል፡፡ በአፍ ግንኙነት የሚያደርገው ሰው ኤችአይቪ ቫይረስ ካለበት ቫይረሱ ከአፍ ወደ የሽንት ቧንባ፣ የሴት ብልት እና ፊንጢጣ ሊተላለፍ ይችላል፡፡
በአፍ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና ሌሎች አባላዘር በሽታዎች ተጋላጭነት
በአፍ በሚደረግ የተራክቦ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ከኤችአይቪ ቫይረስ በተጨማሪ ለቂጥኝ፣ ጨብጥ፣ ኸርፕስ፣ ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ፣ ሄፕታይተስ ኤ እና ቢ ቫይረስ እና ለአሜባ ያጋልጠናል፡፡
ተጋላጭነትን እንዴት መቀነስ ይቻላል
- በአፍ በሚደረግ ግንኙነት ወቅት ማለስለሻ የሌላቸውን ኮንዶም እና ዴንታል ዳም መጠቀም
- በአፍ በሚደረግ ግንኙነት ወቅት የወሲብ ጓደኛችን የዘር ፈሳሽ አፍ ላይ እንዳይፈስ መጠንቀቅ
- ኤችአይቪ ቫይረስ ካለብን በወቅቱ የፀረ ኤችአይቪ ቫይረስ መድኀኒት እየተከታተሉ መውሰድ
- ለሄፒታይተስ ቫይረስ ክትባት መውሰድ
- የግል ንጽህናን መጠበቅ

