ስለኮንዶም አንዳንድ እውነታዎች
ትክክለኛ እና ዘላቂ የኮንዶም አጠቃቀም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ከሚተላለፉ የአባለዘር እና ኤችአይቪ ቫይረስን ለመከላከል ይረዳል፡፡ ነገር ግን ኮንዶምን ብቻ መጠቀም ከነዚህ በሽታዎች ፈጽሞ አይከላከልም ፡፡ አስተማማኙ የመከላከያ መንገድ እራስን ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ማቀብ ወይም ደግሞ በአንድ የፍቅር ጓደኛ ተወስኖ መኖር ነው፡፡
ኮንዶም የአባላዘር በሽታዎችን እና ኤድስን የመከላከል ብቃቱ በላቦራቶሪ እና በኢፒዲሞሎጂካል ጥናት ከፍተኛ ምርምር ተደርጎበታል፡፡ኮንዶም በጣም ጠቃቅን የሆኑትን የአባለዘር በሽታ አምጪ ተዋሕስያንን ሳይቀር የመከላከል ብቃቱ ከፍተኛ እንደሆነ የላቦራቶሪ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
ኮንዶም ከሚጠቀሙ እና ከማይጠቀሙ መካከል የሚጠቀሙት በበሽታ የመያዝ እድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ እንደሆነ የኢፒዲሞሎጂክ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ በተያየዝም ኮንዶም መጠቀም የአባላዘር በሽታዎችን መተላለፍ ቀንሷል፡፡ኮንዶም በተለያየ ደረጃ የአባላዘር በሽታዎችን መከላከል ሲያስችል ይህም የሚወሰነው በዛ በበሽታ የመተላለፍያ መንገድ ነው፡፡ የወንድ ኮንዶም ሙሉ ለሙሉ የቆዳ ንክኪን ላይከላከል ስለሚችል በቆዳ ንክኪ ከሚመጡት የአባላዘር በሽታዎች (ጄኒታል ኸርፕስ፣ ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሸን፣ቂጥኝ እና ከርክር) ይልቅ በመራቢያ አካል ፈሳሽ አማካኝነት የሚተላለፉትን የአባላዘር በሽታዎች (ጨብጥ፣ ክላማይዲያ፣ ትራይኮሞኒያሲስ እና ኤችአይቪ ኢንፌክሽን) ይበልጥ ይከላከላል፡፡
ኤችአይቪ ኢንፌክሽን
ትክክለኛ እና ዘላቂ የኮንዶም አጠቃቀም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ከሚተላለፍ የኤድስ በሽታ አምጪ ከሆነው ኤችአይቪ ቫይረስ ይከላከላል ፡፡ትክክለኛ እና ዘላቂ የኮንዶም አጠቃቀም እንደ ጨብጥ፣ ክላማይዲያ፣ ትራይኮሞኒያሲስ እና ኤችአይቪ ኢንፌክሽን የመሳሰሉትን በመራቢያ አካል ፈሳሽ አማካኝነት የሚተላለፉትን የአባላዘር በሽታዎች ይከላከላል፡፡
ትክክለኛ እና ዘላቂ የኮንዶም አጠቃቀም እንደ ጄኒታል ኸርፕስ፣ቂጥኝ እና ከርክር ያሉ በብልት አካል ቁስለት የሚተላለፉ የአባላዘር በሽታዎችን መተላለፍ ይቀንሳል ይህም የሚሆነው የቆሰለው የብልት ቆዳ ክፍል ሙሉ ለሙሉ በኮንዶም ከተሸፈነ ብቻ ነው፡፡
ትክክለኛ እና ዘላቂ የኮንዶም አጠቃቀም እንደ ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሸን እና ተዛማጅ በሽታዎችን( ጄኒታል ዋርት እና የማህፀን በር ነቀርሳ) ሊከላከል ይችላል፡፡ዘላቂ ያልሆነ አልያም ጭራሹኑ ኮንዶም አለመጠቀም በአንድ የወሲብ ግንኙነት ብቻ የአባላዘር በሽታ ከታመመ ሰው ወደ ጤነኛ ሰው ሊተላለለፍ ይችላል፡፡
አግባብ የሌለው የኮንዶም አጠቃቀም የምንለው ኮንዶምን ሙሉ በሆነው የወሲብ ግንኙነት ወቅት መጠቀም ሳንችል ስንቀር ነው ይህም የኮንዶም መቀደድ፣ ማሟለጭ እና ማዠትን ያካትታል፡፡
ትክክለኛ እና ዘላቂ የኮንዶም አጠቃቀም ዘዴ
ለእያንዳንዱ በሴት ብልት፣ በፊንጢጣ እና በአፍ ለሚደረጉ የወሲብ ግንኙነቶች አዲስ ኮንዶም መጠቀም አለብን ይህም የሚሆነው ኮንዶሙን በቆመ የወንድ ብልት ላይ ካጠለቁ በኋላ ከወሲብ ግንኙነቱ ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ በጠቀም ነው፡፡
የኮንዶሙን ሽፋን በጥንቃቄ ከከፈቱ በኋላ የኮንዶሙን ጫፍ በጣት በመያዝ ኮንዶሙን በቆመ የወንድ ብልት ላይ ማጥለቅ፡፡
ከግንኙነት በኋላ የኮንዶሙን ዘርፍ በመያዝ ኮንዶሙን በጥንቃቄ የዘር ፈሳሹን ሳያፈሱ ከቆመው የወንድ ብልት ላይ ማወለቅ ያስፈልጋል፡፡
የተጠቀምንበትን ኮንዶም በመጸዳጃ ቤት ወረቀት በመጠቅለል ወደ ቆሻሻ መጣያ መጣል ያስፈልጋል፡፡
በማንኛውም የወሲብ ግንኙነት ወቅት የኮንዶሙ መቀደድ ከተሰማን ወዲያውኑ ኮንዶሙን አውልቆ በአዲስ ኮንዶም መቀየር አለብን፡፡
በፊንጢጣ እና በሴት ብልት ለሚደረጉ የወሲብ ግንኙነቶች በቂ የሆነ ውሃ ነክ ማልሰለሻ መጠቀምን መርሳት የለብንም፡፡ ቅባት ነክ ማለስለሻ ማለትም እንደ ቫዝሊን፣ የንጥረ-ነገር ቅባት፣ የመታሻ ፣ የሰውነት ቅባቶች እና የምግብ ዘይቶችን መጠቀም የኮንዶም ማዳከም እና መቀደድን ያመጣል፡፡

