Share

ሄፕታይተስ

ቫይራል ሄፕታይተስ ምንድን ነው?

ቫይራል ሄፓታይተስ በበርካታ ቫይረሶች ምክንያት የሚመጣ የጉበት ቁስል ነው ከእነዚህ ቫይረሶች መካከል ሄፓታይተስ ኤ፣ ሄፓታይተስ ቢ እና ሄፓታይተስ ሲ የተለመዱ ሲሆኑ  ሦስቱም የቫይረስ ዓይነት ተመሳሳይ ምልክቶች የሚያሳዩ ቢሆንም እያንዳንዱ ቫይረስ በተለያዩ መንገዶች የሚተላለፋል ናቸው፡፡

የተመሳሳይ ጾታ እና የሁለቱም ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ለሄፓታይተስ ቫይረስ ተጋላጭ ናቸውን?

አዎ አዋቂዎች ላይ ከሚታየው አዲስ የሄፓታይተስ ኤ ቫይረስ ኢንፌክሽን ውስጥ 10 በመቶ የሚሆነው እና እንዲሁም አዲስ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ኢንፌክሽን ውስጥ 20 በመቶ የሚሆነው በተመሳሳይ ጾታ እና የሁለቱም ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ላይ ይገኛል፡፡   ተጋላጭነትን ከፍ የሚያደርጉ የግንኙነት አይነቶችን የሚያደርጉ የተመሳሳይ ጾታ እና የሁለቱም ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ደግሞ ለሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ ተጋላጭ ናችው፡፡

መርፌን እና ስለታማ ነገሮችን መጋራት የሄፓታይተስ ቢ፣ የሄፓታይተስ ሲ እና የኤችአይቪ ቫይረስ ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡ የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸው ከሚገኝ ሰዎች መካከል 10 በመቶ ያህሉ የሄፓታይተስ ቢ እና 25 በመቶ ያህሉ ደግሞ የሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ ይኖርባቸዋል፡፡  ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በኤች አይ ቪ የተያዙ እና ብዙ የወሲብ ጓደኛ ያላቸው የተመሳሳይ ጾታ እና የሁለቱም ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ለሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ ተጋላጭ ናችው፡፡

ቫይራል ሄፓታይተስ እንዴት ይተላለፋል?

  • ሄፓታይተስ ኤ ቫይረስሄፓታይተስ ኤ ቫይረስ በተበከለ አይነ ምድር ይተላለፋል፡፡ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርጉ ወንዶች ላይ ደግሞ በአፍ እና በፊንጢጣ በሚደረግ ግንኙነት (ሪሚንግ) እና በጣት በሚደረግ ግንኙነት( ፊንገሪንግ) ይተላለፋል፡፡ ሄፓታይተስ ኤ ቫይረስ በአይነ ምድር በተበከለ ምግብ እና ውሃም ይተላፋል፡
  • ሄፓታይተስ ቢበአብዛኛው ጊዜ በበሽታው የተጠቃ ሰው የሰውነት ፈሳሽ ወደ ጤነኛ ሰው ሲገባ የሚተላለፍ ነው። የ ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ከኤችአይቪ አንፃር 50-100 እጥፍ ተላላፊ ሲሆን በቀላሉ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ይተላለፋል፡፡ ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ መርፌ እና ሌሎች ስለታም ነገሮችን በመጋራትም ይተላለፋል፡፡
  • ሄፓታይተስ ሲበዋነኝነት የሚተላለፍው በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር መርፌ እና ስለታም ነገርችን በመጋራት ሲሆን ሌላው ደግሞ ንፅህናን ባልጠበቁ መሳሪያዎች መነቀስ እና ሰዉነትን መበሳት ለበሽታው መተላለፊያ መንገዶች ናቸው። በተወሰነ መልኩ  ሄፓታይተስ ሲ በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ሊተላለፍ ይችላል፡፡በአባላዘር በሽታዎች እና ኤችአይቪ መያዝ እና ከአንድ በላይ የወሲብ ጓደኛ መያዝ ለሄፓታይተስ ሲ ያለንን ተጋላጭነት ይጨምራል፡፡ከሄፓታይተስ ኤ እና ቢ ራስህን ለመጠበቅ ከሁሉ የተሻለው መንገድ መከተብ ነው፡፡

አንድ ስው በሄፓታይተስ ቫይረስ መያዙን እንዴት ማወቅ ይችላል?

በሄፓታይተስ ቫይረስ መያዝን ለማወቅ ቀላሉ መንገድ የደመ ምርመራ ማድረግ  ነው። በጣም ብዙ ሰዎች ምልክቶቹ አይታይባቸውም፡፡ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ አይነት ላይ የሚወሰን አንድ ወይም ከዚያ በላይ የደም ምርመራ ሊያደርጉ ይችላሉ።

ቫይረል ሄፐታይተስ ምን ያህል አስጊ ነው?

ሄፓታይተስ ኤ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ኢንፌክሽን ነው እሱም ከ6ወር ላይበልጥ ይችላል። በሄፓታይተስ ኤ የተያዙ አብዛኛዎቹ አዋቂዎች ለጥቂት ወራት የሕመም ስሜት የሚሰማቸው ሲሆን ያለምንም ዘላቂ የጉበት ጉዳት ሙሉ በሙሉ ይድናሉ፡፡ አልፎ አልፎ ቢሆንም ሄፓታይተስ ኤ የጉበት ቁስለት  እና ሞት ሊያስከትል ይችላል፡፡

ሄፐታይተስ ቢ እና ሄፒታይተስ ሲ ደግሞ አጣዳፊ በሽታዎች ሊሆኑ ሲችሉ እያንዳንዳቸውም ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ የጉበት ኢንፌክሽን ሊያመጡ ይችላሉ። ከአመታት በኋላ ከ15-25 በመቶ የሚሆኑት እነዚህ ሕመምተኞች ለከፍተኛ የጉበት በሽታዎች የሚዳረጉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የጉበት ቁስለት፣ የጉበት ጠባሳ፣ ሙሉ ለሙሉ የጉበት ስራ ማቆም እና የጉበት ካንሰር ይገኙበታል፡፡

ቫይራል ሄፓታይተስ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

በቫይራል ሄፓታይተስ የተጠቁ ስዎች ብዙ ጊዜ ምልክት ስለማያሳዩ በበሽታው እንደተጠቁ ማወቅ አይችሉም።    አጣዳፊ የሄፒታይተስ ምልክቶች አብዛኛውን ጊዜ በርካታ ሳምንታት ወይም ወራት ውስጥ የሚታዩ ሲሆን እስከ 6 ወራት ድረስ ሊቆይ ይችላል።

ለረጅም ጊዜ የቆዩ የሄፓታይተሰስ በሽታዎች ምልክት ለማሳየት ዓመታት የሚፈጁ ሊሆን ስለሚችል ሰዎች ያለምንም የሕመም ስሜት ለብዙ ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ ነገርግን ምልክት በሚያዩበት ወቅት ምልክቶቹ የመጨረሻ ደረጃ የጉበት ሕመም ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የቫይራል ሄፓታይተስ የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያካትቱ ይችላሉ እነርሱም ትኩሳት፣ድካም፣የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ማቅለሽለሽ፣ማስታወክ፣የሆድ ህመም፣ጥቁር ሽንት፣ግራጫ ቀለም ሰገራ፣የመገጣጠሚያ ሕመም እና የቆዳ ቢጫ መሆን ይገኙበታል፡፡

ቫይራል ሄፓታይተስን እንዴት ይታከሙታል?

ሐኪሞች አብዛኛውን ጊዜ እረፍት፣ በቂ ምግብ፣ ፈሳሽ እና በአንዳንድ ሁኔታዎች ፀረ-ቫይረስ መድኀኒት በመስጥት ያክማሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች  ሄፓታይተስ ቫይረስ ሕመምተኞች ሆስፒታል እንዲተኙ ይመከራል።

በአሁኑ ሰዐት ቫይረሱን ለመቆጣጠር እና በጉበት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነሰ ሕክምናዎች በመሰጠት ለይ ይገኛሉ።

የተመሳሳይ ጾታ እና የሁለቱም ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ክትባት ያስፈልጋቸዋል?

አዎ ባለሙያዎች ሁሉም የተመሳሳይ ጾታ እና የሁለቱም ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ለሄፓታይተስ ኤ እና ለሄፓታይተስ ቢ ክትባት  እንዲወስዱ የሚመክሩ ሲሆን ክትባቶቹ በተናጠል ወይም ጥምር ክትባት ሊሰጥ ይችላል። ክትባቶችም ውጤታማ ሲሆኑ ለረጅም ጊዜ የመከላከል አቅም እንዲኖረው ክትባቱ በተከታታይ መውሰድ አለብን፡፡

ሄፓታይተስ ሲ ለመከላከል ከሁሉ የተሻለው መንገድ መርፌ እና ስለታም ነገሮችን አለመጋራት እና ለቫረሱ ከሚያጋልጡን ባህርያት መቆጠብ ነው፡፡ ሄፓታይተስ ሲ ምንም አይነት ክትባት የለውም፡፡

Share

Discover more from Addis Alliance

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading