ውሃ ነክ ማለስለሻዎች ምንድን ናቸው?
WATER-BASED LUBRICANTS
ውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) ምንድን ናቸው?
ውሃ ነክ ማለስለሻ( water-based lubricant) ማለት በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ የምንጠቀመው ማለስለሻ ሲሆኑ በግንኙነት ወቅት የሚፈጠረውን ፍትጊያ እና መቆጥቆጥን የሚቀንስ ፈሰሽ ነው፡፡ ውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) የሚሰሩት ከውሃ፣ ግላይሴሪን እና ከፀረ-ተህዋስያን ንጥረ-ነገሮች ሲሆን አጠቃቀማቸው ቀላል፣ የማይቆጠቁጡ እና ለማጽዳት የማያስቸግሩ ስለሆኑ ከኮንዶም ጋር ለመጠቀም የመከራሉ፡፡
ውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) ከ ቅባት ነክ ማለስለሻዎች (oil-based lubricants) በምን ይለያሉ ?
ለውበት መጠበቅያ እንደ የቆዳ ቅባቶች፣ ቫዝሊን፣ የመታሻ ቅባት፣ የሕፃን ገላ ቅባት፣ የጸጉር ቅባት እና ጄል እና ለምግብነት የምናውላቸው ዘይቶች ባጠቃላይ ቅባት ነክ ማለስለሻዎች ናቸው፡፡ ቅባት ነክ ማለስለሻዎች የኮንዶም መሳሳትን እና በግንኙነት ወቅት መቀደድን ሊያመጡ ስለሚችሉ ከኮንዶም ጋር ለመጠቀም አይመከሩም፡፡ የትኛውም ቅባት ነክ ማለስለሻዎች ከአባላዘር በሽታዎች እና ከኤችአይቪ ቫይረስ አይከላከሉም፡፡
የውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) ጥቅም
- በፊንጢጣ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ምቾት ይጨምራል
- በማለስለሻ እጥረት ምክንያት የሚመጣውን ፊትግያ፣ ሕመም እና መቆጥቆጥ ይቀንሳል
- የብልት አካሎችን መላጥ እና መጎዳት ይቀንሳል
- የኮንዶም መሳሳት እና መቀደድን በመከላከል ጥንቃቄ የሞላው የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንዲኖር ይረዳል
- በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የሚሰማንን አስደሳች ስሜት ይጨምራል
- ጥንቃቄ የሞላው የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና ኮንዶም አጠቃቀምን በማስቻል ጤናማ የወሲብ ሕይወት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
ስለ ማለስለሻዎች የተሳሳቱ ግንዛቤዎች
- እንደ የሕፃናት ገላ ቅባት እና የገላ ቅባት የመሳሰሉት ከኮንዶም ጋር መጠቀም እንችላለን
ስህተት ኮንዶም የተሰራው ላቴክሰ ከሚባል ግብአት ሲሆን ከላይ የጠቀስናቸው ቅባት ነክ ማለስለሻዎች የኮንዶም መሳሰትን እና መቀደድን የስከትላሉ ሲለዚህም ከኮንዶም ጋር ሁሌም መጠቀም የለብን ውሃ ነክ ማለስለሻዎችን (water-based lubricants) ብቻ ነው፡፡
- ማለስለሻዎችን ከተጠቀምን ኮንዶም መጠቀም አያስፈልግም
ስህተት የትኛውም የማለስለሻ አይነት ከአባላዘር በሽታች እና ከኤችአይቪ ቫይረስ አይከላከሉም ሲለዚሀ ኮንዶም ከውሃ ነክ ማለስለሻ ጋር መጠቀም ያስፈልጋልለ፡፡
- ኮንዶም ከውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) ጋር መጠቀም ኤችአይቪ ቫይረስን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡
ትክክል ኮንዶምን በአግባቡ እና በዘላቂነት ከውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) ጋር መጠቀም ኤችአይቪ ቫይረስን ብሎም ሌሎች የአባላዘር በሽታዎችን ለመከላከል የጠቅማል፡፡
- ውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) የቅንጦት ስለሆነ አንዳንዴ ብቻ እንጠቀምበታለን
ስህተት ውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) ለማንኛውም በፊንጢጣ ለሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አስፈላጊ ነው::
- ውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) ለመጠቀም አስቸጋሪ ናቸው
ስህተት በማለስለሻዎቹ ሽፋን ላይ የተጻፈውን አጭር መመርያ በመከተል በቀላሉ መጠቀም ይቻላል፡፡ ይህም ኮንዶሙን በቆመ የወንድ ብልት ላይ ካጠለቁ በኋላ ውሃ ነክ ማለስለሻውን (water-based lubricants) በመቀባት እና ማለስለሻውን በፊንጢጣ ውስጥ በማስገባት መጠቀም ነው፡፡
- ውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) መጥፎ ጠረን እና የሰውነት መቆጣት(አለርጂ) ያመጣሉ
ስህተት አብዛኛዎቹ ውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) ጠረን አልባ ሲሆኑ በተለያዩ ተስማሚ መዐዛ የተሰሩም አሉ ነገር ግን ምንም አይነት የሰውነት መቆጣት(አለርጂ) አያመጡም፡፡
- ከፍቅር ጓደኛዬ ጋር ምራቅ ብጠቀም ችግር የለውም
ሰህተት ውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) ከምራቅ ይልቅ ለረጅም ሰአት የሚቆዩ እና ምቾት የሚሰጡ ሲሆን አስደሳች የግብረ-ስጋ ግንኙነት እንድናድርግ ይረዱናል፡፡
ለአባላዘር በሽታዎች እና ኤችአይቪ ቫይረስ ተጋላጭነትን መቀነሻ መንገዶች
- የወሲብ ጓደኛዎችን ቁጥር መቀነስ የእንዳንዱን የወሲብ ጓደኞችን የወሲብ ታሪክ እና የኤችአይቪ ውጤታቸውን ልናውቅ ስለማንችል የወሲብ ጓደኛዎችን ቁጥር በመቀነስ ያለንን ተጋላጭነት መቀነስ እንችላለን፡፡
- ትክክለኛ እና ዘለቄታዊ ኮንዶም አጠቃቀም ኮንዶምን ከውሃ ነክ ማለስለሻዎች (water-based lubricants) ጋር በትክክል እና በዘለቃታዊ መልኩ መጠቀም ይህም በእያንዳንዱ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ድረስ ከተጠቀምን በለአባላዘር በሽታዎች እና በኤችአይቪ ቫይረስ የመያዝ እድላችንን በእጅጉ መቀነስ እንችላለን፡፡
- በየጊዜው የኤችአይቪ ቫይረስ ደም ምረመራ ማድረግ::
- ለአባላዘር በሽታዎች በጊዜ ሕክምና ማግኘት – የትኛውም አይነት የአባላዘር በሽታዎች ምልክት ከታየብን በጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ሕክምና ማግኘት፡፡

