ኤች አይ ቪ ስላለብኝ በአእምሮዬ ጤንነት ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?
የኤች.አይ.ቪ / ኤድስ ወረርሽኝ በ 80ዎቹ እና 90ዎቹ ውስጥ መላ ትውልድ አጥፍቷል ፡፡ በዛሬው ጊዜ አንድ ሰው በኤችአይቪ በመያዙ አስደንጋጭ ቢሆንም የሞት ፍርድ መሆኑ ግን ቀርቷል። የኤችአይቪ ሕክምና ከመቼውም ጊዜ ተሻሽሏል መድሃኒቱም ሌሎች የሚያስከትላቸውን ህመሞች ቀንሷል። ሆኖም ግን በበሽታው መያዝ አሁንም ድረስ በአስከፊ መንገድ የሰውን ሕይወት እና የአእምሮ ጤንነትን ይነካል ፡፡
እያንዳንዱ ሰው እንደየአቀባበሉ ኤች.አይ.ቪ በመያዙ የተለያየ አይነት ምላሽ ያሳያል። አንዳንዶች እፍረት ፣ ድብርት ወይም ጭንቀት ሲያሳዩ ሌሎች ደግሞ እፎይታ ወይም እረፍት ይመስላቸዋል። ውስጣችንን በማዳመጥ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ስላለብን በአእምሮ ጤንነታችን ፣ ከሰው ጋር በምናደርገው ግንኙነት ወይም በራስ መተማመናችን ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሆነ እና እንዳልሆነ በደንብ እናጥናው።
ማስታወስ ያለብን ነገር ቢኖር ከቫይረሱ እንደምንኖር ያወቅነው በቅርቡም ሆነ ቆየት ብሎ ምን ጊዜም ብቻችንን እንዳልሆንን እና ድጋፍ ልናገኝ እንደምንችል ነው።
ይህ ቀጣይነት የሚገባው የውይይት ርዕሰ ጉዳይ ነው እናም ዛሬ በኤች አይ ቪ ተይዞ መገለል ለማስቆም በጋራ እንደምንሰራ ተስፋ እናደርጋለን ፡፡
How can being HIV+ affect my mental health?
The HIV/AID epidemic wiped out an entire generation in the 80s and 90s. Today, while becoming HIV+ can still be a traumatic event in a person’s life, it no longer has to be a death sentence. HIV treatment has improved and there are fewer drug side effects. However, becoming positive can still affect a person’s life and mental health in a meaningful way.
Each person will have a unique reaction to becoming positive. For some, there will be a shame, depression, or anxiety. For others, it may seem like a relief. Listen to yourself and be really honest about whether or not becoming positive has an impact on your mental health, relationships, or self-esteem.
It’s important to remember that whether you’re newly diagnosed or have been living with HIV for a while, there is support out there and you are not alone.
This is a topic that deserves continued conversation and hopefully, we can work together to end the stigma around living with HIV today.

