Share

ሲጋራ ማጨስ የሚያስከትላቸው የጤና ጠንቆች

ሲጋራ  ማጨስ በአጠቃላይ የጤናችንን ሁኔታ  ይጎዳል፤ በስራ፣በትምህርት እና በማኀበራዊ ሕይወታችን ላይ አሉታዊ ችግሮችን ይፈጥራል፡፡

  • የልብ በሽታን ተጋላጭነት በአራት እጥፍ ይጨምራል፡፡
  • የደም መርጋት በሽታ ተጋላጭነትን በአራት እጥፍ ይጨምራል፡፡
  • የሳንባ ካንሰር ተጋላጭነትን በሃያ አምስት እጥፍ ይጨምራል፡፡
  • የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅምን ይቀንሳል፡፡
  • የጥርስ፣ምላስ እና የአፍ በሽታዎችን ያመጣል፡፡

ሲጋራ ማጨስ በመተንፈሻ ስርአት አካሎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት

  • የሳንባ ካንሰር ያመጣል፡፡
  • የመተንፈሻ ትቦ እና ጥቃቅን ህብረ  ህዋሳት በማጥበብ የማይድን የሳንባ ሕመም ያስከትላል ይህም ሕመም ለሞት ያደርሳል፡፡
  • አስም ላለባቸው ሰዎች አስምን ያባብሳል በቀላል ሕክምና ለመዳን ያዳግታቸዋል፡፡

ሲጋራ ማጨስ ተጋላጭነትን የሚጨምራቸው የካንሰር አይነቶች

  • የሽንት ፊኛ
  • የደም
  • የማሕፀን በር
  • የአንጀት
  • የጉሮሮ
  • የኩላሊት እና የሽንት ትቦ
  • የጉበት
  • የአፍና ተዛማጅ የሆኑ የሰውነት አካላት
  • የቆሽት እና
  • የጨጓራ ካንሰር ናቸው፡፡

ሲጋራ ማጨስ በስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት

በሴቶች ላይ

  • ቀኑ ያልደረሰ ልጅ መውለድ
  • በማሕፀን ውስጥ የፅንስ መሞ ት
  • አነስተኛ ክብደት ያለው ልጅ መውለድ
  • ከማሕፀን ውጭ እርግዝና
  • የፅንስ አካል ጉዳት

በወንዶች ላይ

  • የወንድ የዘር ፈሳሽ መጠን መቀነስ ያስከትላል፡፡

Share

Discover more from Addis Alliance

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading