Share

ኮሮና ቫይረስ

ኮሮና ቫይረስ

ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?

በጣም የተለመዱት የCOVID-19 ምልክቶች ትኩሳት ፣ ድካም እና ደረቅ ሳል ናቸው ፡፡ አንዳንድ ሕመምተኞች ላይ ደግሞ ባልተለመደ መልኩ ቁርጥማት፣ የአፍንጫ መደፈን ፣ የአፍንጫ ፈሳሽ ፣ የጉሮሮ መሰርሰር ወይም ተቅማጥ ሊኖራቸው ይችላል ፡፡ እነዚህ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ መለስተኛ ሆነው እና ቀስ በቀስ ይጀምራሉ ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በበሽታው ይያዛሉ ነገር ግን ምንም ምልክት አያሳዩም እንዲሁም ህመም አይሰማቸውም። ብዙ ሰዎች (80% ገደማ የሚሆኑት) ልዩ ህክምና ሳያስፈልጋቸው ከበሽታው ያገግማሉ ፡፡ ከ COVID-19 ከሚያዙ ከስድስቱ ሰዎች ውስጥ አንድ ሰው በጠና ታሞ የመተንፈስ ችግር ያዳብራሉ ፡፡ አዛውንቶች ፣ እና እንደ የደም ግፊት ፣ የልብ እና የመተንፈሻ አካል ችግር ወይም የስኳር ህመምን የመሰሉ መሰረታዊ ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች በበሽታው በጠና የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው ፡፡ ትኩሳት ፣ ሳል እና የመተንፈስ ችግር ምልክት የገጠማቸው ሰዎች የሕክምና ክትትል በቶሎ ማግኘት ይገባቸዋል ፡፡

መተላለፊያ መንገዶቹ ምንድናቸው?

ሰዎች ቫይረሱ ካለባቸው ሌሎች ሰዎች በCOVID-19 ሊያዙ ይችላሉ ፡፡ በሽታው ያለው ሰው ሲያስነጥስ ወይም ወደውጭ ሲተነፍስ ከአፍንጫ ወይም ከአፍ በሚወጡ በጣሙን ጥቃቅን ጠብታዎች በኩል ከሰው ወደ ሰው ሊሰራጭ ይችላል ፡፡ እነዚህ ጠብታዎች በሰውዬው ዙሪያ ባሉ ነገሮች እና ገጽታዎች ላይ ያርፋሉ ፡፡ ሌሎች ሰዎች እነዚህን ዕቃዎች ወይም ገጽታዎች ነክተው ዐይኖቻቸውን ፣ አፍንጫቸውን ወይም አፋቸው በሚነኩበት ጊዜ በCOVID-19 ቫይረስ ይይዛሉ ፡፡ እንዲሁም COVID-19 ያለበት ሰው ወደውጭ በሚተነፍስበት ወቅት ወይም በሚያስልበት ጊዜ በቅርብ ያሉ ሰዎች ወደውስጥ ሲተነፍሱ በCOVID-19 ሊያዙ ይችላሉ ፡፡ ከታመመ ሰው ከ 1 ሜትር ራቅ ማለት አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው ፡፡

እራሶን ለመጠበቅ ምን ምን ማድረግ ይገባዎታል?

  • የእጅ ንኪኪን ይቀንሱ አልያም ያስወግዱ፡፡
  • በመደበኛነት እና በአግባቡ እጆችዎን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ከ20-40 ሰከንድ ያህል ይታጠቡ።
  • በእራስዎ እና በሚያስነጥስ ወይም በሚያስል ማንኛውም ሰው መካከል ቢያንስ 1 ሜትር ርቀት ይኑር፡፡
  • አይኖችዎን ፣ አፍንጫዎን እና አፍዎን ከመነካካት ይቆጠቡ፡፡ • በሚያስነጥሱበት ወይም በሚያስሉበት ጊዜ አፍዎን እና አፍንጫዎን እጆን በማጠፍ በክርኖ ወይም በሶፍት መሸፈን አለብዎት ፡፡
  • ህመም ከተሰማዎት ቤት ውስጥ ይቀመጡ ፡፡ ትኩሳት ፣ ሳል እና የመተንፈስ ችግር ካለብዎ የህክምና እርዳታ ይፈልጉ፡፡ ወደህክምና ተቋም ከመሄዶ በፊት አስቀድመው ይደውሉ ፡፡ የአካባቢዎ የጤና ባለስልጣን የሚሰጥዎትን መመሪያዎችን ይከተሉ፡፡ በነፃ የስልክ መስመር 8335 በመደወል መረጃን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • የሚቻል ከሆነ ከቦታ ቦታ ከመጓዝ ይቆጠቡ፤ በተለይም አዛውንት ከሆኑ ወይም የስኳር በሽታ ፣ የልብ ወይም የመተንፈሻ አካላት በሽታ ካለብዎ በበሽታው የመጎዳት እድሎ ከፍ ስለሚል ከሰዎች ጋር ያሎትን ግንኙነቶች ይቀንሱ፡፡
  • ግዴታ ካልሆኖቦት ብዙ ህዝብ ሚሰበሰብበት ቦታ߹ እንደ ጭፈራ ቤት ያሉ የተፋፈጉ ቤቶች እንዲሁም ሺሻ ቤቶች ከመሄድ ይቆጠቡ፡፡ ሺሻን ተጋርቶ በአንድ ላይ ማጨስ በትንፋሽ የሚወሰድ እንደመሆኑ ለበሽታው ሊያጋልጥ ይችላል፡፡

ምንጭ WHO

 

Share

Discover more from Addis Alliance

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading