ለካንሰር በሽታ የሚያጋልጡን ነገሮች
አውቀንም ይሁን ሳናውቅ በየቀኑ የምናደርጋቸው እና ለካንሰር በሽታ የሚያጋልጡን ነገሮችን ኦልተርኔቲቭ ዌብ ፔጅ ዘርዝሯቸዋል።
1. የላብ ማጥፊያ እና የጠረን መቀየሪያ (ዲዮድራንት)
አብዛኛው የጡት ካንሰር የሚከሰተው የጠረን መቀየሪያ(ዲዮድራንት) ከምናደርግበት የብንታችን አካባቢ ነው። ይህም የሚከሰተው በዲዮድራንት ውስጥ የሚገኘው አልሙኒየም በሚያመጣብን ጠንቅ ሳቢያ ነው ፤ በመሆኑም በቀላሉ በቤት ውስጥ በቀላሉ የሚዘጋጁ የጠረን መቀየሪያ ስልቶችን መጠቀሙ ይበጃል።
ለምሳሌ ሎሚን በአማራጭነት መጠቀም ይቻላል።
2. መርዛማነት ያላቸው የውብት መጠበቂያዎች፦
ቆዳችን መላ አካላችንን የሸፈነ እና በጣም ጥንቃቄ የሚያሻው እንደመሆኑ በፋብሪካ ውስጥ ያለፉ የውበት መጠበቂያ ምርቶችን የቆዳችንን ባህሪይ በሚገባ ሳናውቅ መጠቀም አይመከርም። አብዛኛዎቹ የውበት መጠበቂያዎች የተሰሩበት ንጥረ ነገርም ቆዳን ዘልቆ የመግባት እቅም ያለው ነው። በመሆኑም ተፈጥሯዊ የውበት መጠበቂያ ዘዴዎችን መጠቀሙ እጅግ ተመራጭ መሆኑ ነው የሚነገረው ።
3. በጨረር የሚደረጉ ምርመራዎች፦
በየአውሮፕላን ማረፊያው፣ በየሆስፒታሉ እና በሌሎችም ቦታዎች በጨረር የምናደርገው የጡት ፣ አጠቃላይ የውስጥ አካል ምርመራ ሁሉ ለካንሰር የሚያጋልጠን ግን ብዙም ቁብ ያልሰጠነው ጉዳይ እንደሆነም ነው የተገለፀው።
4. የታሸጉ ምግቦች፦
የታሸጉ ምግቦች የታሸጉበት ንጥረ ነገር በጥንቃቄ ያልተዘጋጀ እንደሆነ በቀላሉ ለካንሰር አጋልጮ ሊሰጠን ይችላል። በተጨማሪም አብዛኛዎቹ የታሸጉ ምግቦች ቢ ፒ ኤ (bisphenol ) ማለትም የአይጦች የአንጎል ሴሎችን ተፈጥሯዊ ሁኔታ የማዛባት አቅም እንዳላቸው በየማሸጊያዎቻቸው ላይ የሚገልፁበት ሁኔታ ነው ያለው።
5. ሳሙናዎች፣ ሻምፑዎች እና ክሬሞች፦
እነዚህ ነገሮች ሽታ፣ ከለር ያላቸው እና በቆዳ፣ በፀጉር ላይ የሚተገበሩ እንደመሆናቸው መጠን አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያሻቸዋል። በተለይም በተሰነጠቀ ቆዳ ላይ ስንጠቀማቸው ጉዳታቸውን የከፋ ልናደርገው እንችላለን። ታዲያ በተቻለ አቅም በተፈጥሯዊዎቹ የንፅህና እና የውበት መጠበቂያዎች መጠቀሙ ራስን ከካንሰር በሽታ ለመጠበቅ ተመራጩ ዘዴ ነው።
6. ከአኩሪ አተር የሚሰሩ ምርቶች፦
ለአብነትም እንደ ሶይ ወተት ያለው ምግብ “ሄማግሉቲኒን” የተሰኘ እና የደም መርጋትን የሚያስከትለው ንጥረ ነገር ተጠቃሽ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ንጥረነገሩ የኤስትሮጅን መጠንን ከፍ በማድረግ ለልብ ህመም የመጋለጥ ዕድላችንን ያሰፋዋል። በመሆኑም ተፈጥሯዊዎቹን የወተት ምርቶች እንዲጠቀሙ ይመከራሉ።
7. ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎች፦
በሶዳ ውስጥ የሚገኘው እና ፍሩክቶስ የተሰኘውን ንጥረ ነገር ጨምሮ በሰው ሰራሽ ሁኔታ የሚዘጋጁ ማጣፈጫዎች አደገኛ እና ለካንሰር በቀላሉ የሚያጋልጡን ነገሮች ናቸው። ከረሜላዎች፣ አንዳንድ የስኳር ምርቶች በዋናነት ለካንሰር ሊያጋልጡን እንደሚችሉም ተነግሯል።
8. ፍሎራይድ የተጨመረበት ውሃ፦
ፈሎራይድ በሰውነታችን የሚገኙ ጠቃሚ ማዕድናትን አጥቦ በማውጣት ተፈጥሯዊ በሽታ የመከላከል አቅማችን ያዳክመዋል። በመሆኑም ፍሎራይድ የተጨመረበት ውሃ ብዙ ጊዜ እንደምናስበው በጣም ጠቃሚ አይደለም ፤ ከዚያ ይልቅ የምንጭ ውሃ (የታሸገ ውሃ) የተሻለ ተመራጭ ልናደርገው ይገባል ነው የተባለው።
9. በምንመገበው ስጋ እና ወተት ውስጥ የሚጨመሩ ሆርሞኖች፦
10. መድሃኒቶች፦
ዶክተርዎን ቢጠይቁት ካንሰርን ለመከላከል ውጤታማው ዘዴ የአኗኗር ዘይቤን መቀየር እንደሆነ ይነግርዎታል። ይህ ትክክል ነው፤ ካንሰርን በመድሃኒት አቅም ማሸነፍም በጣም አስቸጋሪ ነው ። ከዚህ የተሻለው አማራጭ የአመጋገባችን ፣ የስፖርት እንቅስቃሴያችንን ሁኔታ ማስተካከሉ ላይ ነው።

