ሄፕታይተስ ቢ ምንድን ነው?
ሄፕታይተስ ከጉበት መቆጣት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን፥ ከኤድስና ከቲቢ የበለጠ ገዳይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነው፡፡ ሄፒታይተስ አይነቱ ብዙ ሲሆን እንደ ሄፒታይተስ ቢ ሁሉ ሌሎችም አይነት አሉት (ሄፒታይተስ A፣ B፣ C፣ D እና E)። እንደ አጠቃላይ ሂፐታይተስ በኬሚካሎች፣ በእጾች፣ ከመጠን በላይ አልኮል በመጠጣት ወይም በቫይረስ ሊመጣ ይችላል። ሄፕታይተስ ቢ የሚመጣው በሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ነው።
የህመሙ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
ብዙ ሰዎች በሄፕታይተስ ቢ ሲያዙ መጀመሪያ ምንም ዓይነት ምልክት አያሳዩም፤ ከነዚህም መሃል አንዳንዶቹ ከብዙ ዓመታት በኋላ ጉበታቸው ይጎዳል ወይም የጉበት ካንሰር ይይዛቸዋል። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች የበሽታው “ተሸካሚዎች” የሚባሉ ሲሆን ቫይረሱንም ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላሉ።
የህመሙ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊጨምር ይችላል፦
- ቆዳና የዓይን ነጩ ክፍል ቢጫ ይሆናሉ (ጆንዲስ በመባል ይታወቃል)
- ሽንት ጥቁር ይሆናል
- ፊት ይገረጣል
- ድካም ይሰማል
- የሆድ እቃ ህመም ይሰማል
- የምግብ ፍላጎት ይቀንሳል
- ማቅለሽለሽና ማስመለስ
- የመጋጠሚያ (የአንጓ) ህመም
አንድ ሰው ሄፕታይተስ ቢ እንዴት ሊይዘው ይችላል?
የሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ በበሽታው በተያዘ ሰው ደም፣ ጉበት እና የሰውነት ፈሳሽ ውስጥ ይገኛል። ሄፕታይተስ ቢ ተሸካሚ የሆነች ሴት በእርግዝናዋ ወቅት ወይም በወሊድ ግዜ ቫይረሱ ወደ ሕፃኑ ልጅ ሊሰራጭ ይችላል። በአውስትራሊያ ውስጥ ሕፃናት በሙሉ ከተወለዱ በኋላ የሄፕታይተስ ቢ ክትባት ይሰጣቸዋል።
የሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ በሚከተለው ሁኔታም ሊሰራጭ ይችላል፦
- ንጹሕ ባልሆኑ የመርፌ መውጊያ መሳሪያዎች፣ በቀዶ ሕክምና፣ ጥርስ ሲነቀል፣ ወይም በመነቀስ
- የሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ያለው የሰው ደም ሲሰጥዎት። በብዙ አገራት ለሰዎች የሚሰጥ ማንኛውም ደም (Blood transfusion) ከሂፐታይተስ ቢ ነፃ ለመሆኑ ይመረመራል።
- ሄፕታይተስ ቢ ያለው ሰውን እቃዎች ለምሳሌ ምላጩንና የጥርስ ብሩሹን (ደም ያለበት ሊሆን ይችላል) በመጠቀም።
- ሄፕታይተስ ቢ ካለው ሰው ጋር ያለኮንዶም የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ።
ሄፕታይተስ ቢን እንዴት ነው መመርመር የሚቻለው?
- ከዚህ ቀደም የሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ይዞዎት እንደሆነ በደም ምርመራ ለማወቅ ይቻላል።
- የደም ምርመራው ቫይረሱ ከሰውነትዎ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ እንደሆነ ያሳያል። ቫይረሱ ከሰውነትዎ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የተወገደ ቢሆንም የሄፕታይተስ ቢ አንታይ-ቦዲስ (በሽታ እንዳይዘን የሚዋጉ ፕሮቲኖች) በሰውነትዎ ውስጥ ይገኛሉ።
- ምርመራው እስካሁን የሄፕታይተስ ቢ ተሸካሚ መሆንዎትን ካረጋገጠ ዶክተርዎ በድጋሚ እንዲመረመሩ ያዛል ወደ ስፔሻሊስት ዶክተሮች ክሊኒክ እንዲሄዱም ይጽፍልዎታል።
- ሄፕታይተስ ቢ ካለው ሰው ጋር ያለኮንዶም የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ።
የሄፕታይተስ ቢ በሽተኛ ከሆኑ የሚከተሉትን በማድረግ ትንሽ ሻል ሊሎት ይችላል፦
- አልኮል መጠጣት ያቁሙ
- የተመጣጠነና ስብ ያልበዛበት ምግብ መመገብ
- ሳያቋርጡ መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ
- ሲደክሞት እረፍት ማድረግ
- ሄፕታይተስ ቢ ካለው ሰው ጋር ያለኮንዶም የግብረ ስጋ ግንኙነት አለማድረግ።
አንድ ሰው ሄፕታይተስ ቢ እንዳይዘው ምን ማድረግ ይኖርበታል?
- ከአዲስ ጓደኛ ወይም የሄፕታይተስ ቢ ክትባት ካለወሰደ ሰው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲያደርጉ ሁል ግዜ ኮንዶም ይጠቀሙ።
- መርፌዎች፣ ስሪንጅ ወይም እጽ/ድራግ/ የመወጊያ መሳሪያዎችን ከሌሎች ጋር በመጋራት አይጠቀሙ።
- የጥርስ ቡሩሽ ወይም ምላጭ ከሌሎች ጋር በመጋራት አይጠቀሙ።
- መከላከያ ካልኖሮት የሄፕታይተስ ቢን ክትባት ይውስዱ፣ ሄፕታይተስ ቢ ካለው ሰው ጋር አብረው የሚኖሩ ሰዎች የሄፕታይተስ ቢ ክትባትን ማግኘት ይኖርባቸዋል።
- የቫይረሱ ተሸካሚ ከሆኑ እናቶች የሚወለዱ ሕፃናት፣ ከተወለዱ በኋላ ሄፕታይተስ ቢ ኢሚኖግሎፕሊን መርፌ በመወጋት ተጨማሪ መከላከያ እንዲያገኙ ይሰጣቸዋል።

