ካሮትና ቀይስር የመመገብ የጤና ጥቅሞች
ካሮት
- የምግብመፍጨትሂደትንያግዛል
ካሮት በፋይበር የበለፀገ ስለሆነ የምግብ መፈጨት ሂደትን በማገዝ እንደ ሆድ ድርቀት ያሉ ችግሮችን እንዳይከሰቱ ያደርጋል። - ለአይናችንየሚሰጠውጥቅምከፍተኛነው
ካሮት በሻይታሚን ኤ የበለፀገ ስለሆን እይታችን የተሻለ እንዲሆን ያግዛል - በሽታንየመከላከልአቅምንያዳብራል
ካሮትን መመገብ በሽታን የመከላከል አቅማችን እንዲዳብርና ጤናማ እንድንሆን ይረዳል - ስትሮክንይከላከላል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በቀን አንድ ካሮትን መመገብ ለስትሮክ ያለንን ተጋላጭነት በ፮፰ % የመቀነስ አቅም አለው። - ካንሰርንይከላከላል
ካሮት በውስጡ በያዛቸው ልዩ ልዩ ንጥረ ነገሮች ምክንያት ካንሰርን የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ።
- የምግብመፍጨትሂደትንያግዛል
ቀይስር
- ለጉበት ጤናማነት
ቀይስር ውስጥ የሚገኝ ቤታይን የተባለ ንጥረነገር የጉበትን አገልግሎት የማነቃቃት አቅም አለው። - ከሳንባ ጋር ተያያዥ ችግሮችን ይከላከላል
ቀይስር ቫይታሚን ሲ በውስጡ ስለያዘ የአስም ምልክቶች እንዳይነሱ ይረዳል፣ በሽታ የመከላከል አቅማችን እንዲዳብርም ያግዛል። ቤታ ካሮቲን የሚባለው ንጥረ ነገር በሳንባ ካንሰር የመጠቃት እድልን ይቀንሳል። - ካታራክትን ይከላከላል
ቤታ ካሮቲን የሚባል ንጥረ ነገርን የያዘው ቀይስር ከእድሜ ጋር ሊመጣ የሚችልን የአይን ሞራ እንዳይከሰት ይከላከላል። - የሃይል መጠንን ይጨምራል
ቀይስር በካርቦሀይድሬት የበለፀገ ስለሆነ ሀይል ሰጭ ከሚባሉት ምግቦች እንዲመደብ ያደርገዋል። - ካንሰርን ይከላከላል
አንዳንድ ጥናቶች ቀይስር ከቆዳ፣ ከሳንባ እና ከአንጅት ካንሰር የመከላከል አቅም እንዳለው ያሳያሉ።
- ለጉበት ጤናማነት

