የሆድ ድርቀት (constipation)
የሆድ ድርቀት የሚከሰተው ትልቁ አንጀት የተመገብነው ምግብ ብዙ ውሃ መጦ ሲያልቅ ነው፡፡ ይሁንና ድርቀትን የሚያመጡት የተለያዩ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል በፋይበር (አሰር) የበለጸጉ ምግቦችን ያለመመገብ፣ ዓይነ ምድር መጣሁ ሲል በወቅቱ አለመጸዳዳት፣ወተትና የወተት ተዋጾዎችን አዘውትሮ መመገብ፣እንቅስቃሴ አለማድረግ በተለይ በዕድሜ የገፉ ሰዎች፣እርግዝና እንዲሁም አንዳንድ እንደ ሳይኮትሮፒክ እና ናርኮቲክ ያሉ መድኃኒቶች ድርቀትን ሊመጡ ይችላሉ፡፡
የድርቀት ምልክቶች ከሆኑት ውስጥ የሆድ ሕመም፣የሆድ ጭብጠት፣የሆድ መንፋት፣ ማቅለሽለሽ እና የመግብ ፍላጎት ማጣት ናቸው፡፡ አብዛኛው ጤነኛ ሰው ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ አይነምድር ይወጣል፡፡ ዓይነ ምድር በውስጡ በቂ እርጥበት ያለው ከመሆኑም በላይ በሚወጣበት ጊዜ ያለአንዳች ስቃይ ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን ለሁለትና ከዚያ በላይ ቀናት መቆየት ዓይነ ምድር ያለመውጣት ችግርን ያመለክታል፡፡
አንዳንድ ጊዜም የደረቀው ዓይነ ምድር ከታችኛው ትልቁ አንጀት ክፍል ተቀርቅሮ ለማስወጣት ስለሚያስቸግር በጣም ማማጥ ወይም መሰርሰር ባስ ሲልም አንጀትን መታጠብ አስፋላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ በዙ ማማጥ ግን የኪንታሮት በሽታ ሊያመጣ ይችላል፡፡
ድርቀትን ለመካከል የመከተሉትን ጠቃሚ ምክሮች ይተግብሩ
- ቀን በተወሰነ ሰዓት ዓይነምድር ለመውጣት ልምድ ያድርጉ
- ሁል ጊዜ ጧት አንድ ብርጭቆ የሎሚ ጭማቂ በሞቀ ውሃ ይጠጡ
- ውሃ በብዛት ይጠጡ
- ጎመን፣ቆስጣ፣ፓፓያ፣ሙዝ እና ሌሎች ቅ
- ለ15 ደቂቃ ዱብ ዱብ ይበሉ
- ዱልኮላክስ ወይም ሌላ ለድርቀት የሚወሰድ ፍሬ ይውሰዱ
- ጠላ ቅጠልና ፍራፍሬዎችን ይመገቡ
- ወደ ሽንት ቤት ከመሄዶ በፊት ፈጠን ባለ ሁኔታ

