ጤና ለሁሉም
አዲስ አሊያንስ ጤናማ እና እራሱን የሚጠብቅ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ማኅበረሰብ እንዲኖር የማድረግ ራእይን ያነገበ በተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወጣት ኢትዮጵያውያን የተመሰረተ ሀገር በቀል ማኅበር ነው፡፡
አዲስ አሊያንስ በሚያዚያ ፳፻፰ ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን አላማውም
የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን የተሟላ ፆታዊ እና የስነ-ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡
ኮንዶም እና ማለስለሻ የሚጠቀሙ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ቁጥርን መጨመር፡፡
እራሱን የሚጠብቅ እና ማንነቱን የተቀበለ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ማኅበረሰብ እንዲኖር ማስቻል፡፡
መሰረታዊ መርሖች
ማጠናከር፡- የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ኅብረተሰብ ተደማጭነት እንዲኖረው እና እያንዳንዱ ግለሰብ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ግንዛቤ ያለው እና እራሱን የቻለ እንዲሆን ማድረግ፡፡
በጋራ መስራት፡- ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ሁሉም የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ማኅበረሰብ በጋራ መትጋት ያስፈልገዋል ይህም እንዲሆን ከአገር በቀል ድርጅቶችም ሆነ፣ከወዳጆች እና ከመንግስት አካለት ጋር በመተባበር ማግኘት የምንችለውን ከፍተኛ ውጤት ለመግኘት መጣር አለብን፡፡
ውጤት ተኮር፡- ተሰሚነት ያለው የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ኅበረተሰብ እንዲኖር የምናደርገው ጥረት ማኅበረሰቡን በማጎልብት ተፈላጊውን ውጤት ማምጣት መቻል አለበት፡፡ ግብአትን በአግባቡ መጠቀም፡- ከአጋር ድርጅቶች እንዲሁም ከማኅበረሰቡ የሚገኙትን ግብአቶች ተጠያቂነት፣ብቃት እና ውጤታማነት ባለው መልኩ መጠቀም ፡፡
ራዕይ
ራዕይ
አዲስ አሊያንስ ጤናማ እና እራሱን የሚጠብቅ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ማኅበረሰብ እንዲኖር የማድረግ ራእይን ያነገበ ሀገር በቀል ማኅበር ነው፡፡
ተልዕኮ
ተልዕኮ
የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን የተሟላ ፆታዊ እና የስነ-ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡
ግብ
ግብ
የተለያዩ መረጃዎቸን በመስጠት እራሱን የሚጠብቅ እና ማንነቱን የተቀበለ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ማኅበረሰብ እንዲኖር ማስቻል፡፡
