ስለ አልኮል መጠጥ ሱሰኝነት አንዳንድ እውነታዎች

የአልኮል መጠጥ ሱሰኝነት ማለት ቀጥሎ  ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑትን ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ካሳየን ነው፡፡ እነርሱም

  • ካሰብነው መጠን በላይ ከጠጣን፡፡
  • የአልኮል መጠጦችን ላለመጠጣት ከአንዴ በላይ ወስነን ነገር ግን ማቆም ካልቻልን፡፡
  • የአልኮል መጠጦችን በመጠጣት ካሰብነው  ጊዜ በላይ ካሳለፍን፡፡
  • የአልኮል መጠጦችን የመጠጣት ከፍተኛ ፍላጎት ከተሰማን፡፡
  • የአልኮል መጠጦችን በመጠጣታችን ምክንያት በመስሪያ ቤት እና በትምህርት ቤት ችግር ከተፈጠረ ወይም ከቤተሰብ አባላት ጋር አለመግባባት እና  ችግር ካስከተለ፡፡
  • ከዚህ በላይ የጠቀስናቸው ችግሮች ከተፈጠሩ በኋላም የአልኮል መጠጦችን መጠጣት  ካላቆምን፡፡
  • የአልኮል መጠጦችን ለመጠጣት ስንል ጠቃሚ የዕለት ተዕለት ተግባራችንን ማከናወን ካቆምን፡፡
  • የአልኮል መጠጦችን  ከጠጣን በኋላ በተደጋጋሚ መኪና የምንነዳ፣ ማሺኖችን የምናንቀሳቅስ፣ ዋና የምንዋኝ፣ አደገኛ በሆኑ ቦታዎች አካባቢ የእግር መንገድ የመናደርግ እና ጥንቃቄ የሌለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያደረግን ከሆነ።
  • የአልኮል መጠጦች ድብርት ፣ ጭንቀት እና የአእምሮ መሳትን ካስከተሉብን በኋላ መጠጣት መቀጠል።
  • የአልኮል ሞቅታ እንዲሰማን ከወትሮ ከፍ ያለ መጠን አልኮል መጠጣት ካስፈለገን።
  • የስካር ስሜት ከለቀቀን በኋላ የእንቅልፍ ማጣት፣ መንቀጥቀጥ፣ድብርት፣ጭንቀት፣እረፍት ማጣት፣ማቅለሽለሽ እና ላብ ማላብ ምልክቶች ከተሰማን።

የአልኮል መጠጥ ሱሰኝነት በሁለት ይከፈላል እነርሱም  ከላይ ከዘረዘርናቸው  ምልክቶች በተጨማሪ ሲሆን

መጠነኛ  ማለትም ለወንድ  ሁለት ፤ ለሴት ደግሞ አንድ የአልኮል መጠጦችን በየቀኑ መጠጣት እና ከፍተኛ ማለትም ላለፉት ሰላሳ ቀናት ውስጥ ለአምስት ቀናት ያክል አምስት እና ከዛ በላይ የአልኮል መጠጦችን ከጠጣን ነው፡፡

የአልኮል መጠጥ ሱሰኝነት በመኖርያ ቤት፣ በስራ ቦታ እና በትምህርት ቤት የሚኖረንን ግንኙነቶች ያስተጓጉልብናል፡፡

የአልኮል ሱሰኝነት ለተለያዩ  የጤና  ጠንቆች ያጋልጣል ለምሳሌ ያህል የጉበት፣የአንጎል፣የኩላሊት በሽታ እና ካንሰር ያመጣል:: ነፍሰ ጡር እናት ላይ ደግሞ የፅንስ ጉዳት ያስከትላል፡፡ የአልኮል መጠጥ ሱሰኝነት ለመኪና እና ለተለያዩ ከባድ አደጋዎችም ያጋልጣል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ካለብዎት ወደ የሰነ ልቦና ሐኪም ጋር በመሄድ ሕክምና ማግኘት ያስፈለጋል፡፡