የልብ ሕመም
የሰውነታችን ክብደት በሚጨምርበት ጊዜ በልባችን ደም ስሮች ውስጥ የስብ መከማቸት ይፈጠራል ይህም ወደልብ ጡንቻ የሚሄደውን ደም በመቀነስ ልባችን የዘወትር ተግባሩን እንዳያከናውን እና ልባችን እንዲደክም ያደርጋል፡፡
የደም ግፊት
ከላይ እንደተጠቀሰው እንደ የልብ ሕመሙ አይነት ክብደታችን በሚጨምርበት ወቅት ስብ በደምስሮች ግድግዳ ላይ ይከማቻል ይህም ደም እንደወትሮው በቀላሉ እንዳያልፍ እና በደም ስር ውስጥ ግፊት እንዲፈጠር ያደርጋል::
የደም መርጋት በሽታ (እስትሮክ)
የደም መርጋት በሽታ የሚከሰተው ከላይ እንደተባለው የደም ስሮችን የስብ ክምችት በሚዘጋበት ጊዜ ከግፊቱ የተነሳ የደም ስሩ ተበጥሶ ደም ወደ አካላችን ይፈስ እና ይረጋል፡፡ ይህም የረጋው ደም ወደ አንጎል የሚሄደውን የደምስር የዘጋ ከሆነ የአንጎላችንን የተወሰነውን ህብረ ህዋስ እንዲሞት ያደርጋል፡፡ በወቅቱ ሕክምና ካልተደረገለት ለሞት አደጋ ያጋልጣል፡፡
የስኳር በሽታ
የስኳር በሽታ ማለት በደማችን ከፍተኛ የሆነ የስኳር መጠን መኖር ሲሆን ይህም የተለያዩ የጤና እክሎች ያስከትላል፡፡የሰውነት ክብደት መጨመር ለከፍተኛ የሆነ የደም ውስጥ የስኳር መጠን ያጋልጣል፡፡
አላስፈላጊ የሰውነት ስብ መከማቸት
በተፈጥሮ ሁለት አይነት የሰውነት ስብ(ኮሌስትሮል) አሉ እነርሱም LDL እና HDL ናቸው፡፡ HDL ጥሩ አይነት የሰውነት ስብ ሲሆን LDL ግን የየደም ግፊት እና ተመሳሳይ በሽታዎ ችን ያስከትላል እናም የሰውነት ክብደት በሚጨምርበት ወቅት የLDL መጠን ይጨምራል፡፡
ነቀርሳ(ካንሰር)
የሰውነት ክብደት መጨመር ለትልቁ አንጀት፣ለጡት፣ለማህጸን እና የሃሞት ከረጢት ነቀርሳ(ካንሰር) ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡
የመገጣጠሚያ ሕመም
የሰውነት ክብደት መጨመር በሰውነታችን መገጣጠሚያዎች ላይ ክብደት ስለሚጨምር የመፋተግ እና ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ሕመም ያስከትላል:: ጉልበት፣የዳሌ እና የወገብ መገጣጠምያዎች በአብዛኛው ይጠቃሉ::
በእንቅልፍ ሰዓት የመተንፈስ ችግር
የሰውነት ክብደት መጨመር ከአንገታችን አካባቢ ያለውን የስብ ክምችት ስለሚጨምር በመኝታ ሰአት የመተንፈስ ችግርን ያስከትላል፡፡
የስነ ተዋልዶ ጤና ችግር
የሰውነት ክብደት መጨመር የወር አበባ መዛባት እና መካንነት ሊያመጠ ይችላል፡፡
የሐሞት ጠጠር
የሐሞት ጠጠር በአብዛኛው የሚሰሩት ከስብ(ኮሌስትሮል)ነው ይህም ስብ ክብደት ሲጨምር አብሮ ይጨምራል፡፡
