Skip to content
- ሴክስ/Sex – ጾታ ማለት ሲሆን ይህንንም በተፈጥሮ የምናገኘው ነው ፡፡
- ጀንደር/ Gender – በአንድ ማኅበረሰብ ባለበት ወይም በሚኖርበት ጊዜ እና ወቅት ላይ ተመርኩዘው የተዋቀሩ የወንድነት ወይም የሴትነት መገለጫ ባሕሪያት ሲሆን፤ ለወንድ እና ለሴት ተብለው የተመደቡ ወይም በዕድገት ግዜ የምንማራቸው ናቸው፡፡ እነዚህ መገለጫ ባሕሪያት በጊዜ እና ባለንበት ማኀበረሰብ መሰረት ሊለያዩ የሚችሉ ሲሆን በተፈጥሮ ወንድ ወይም ሴት ከምንለው የጾታ (Sex) መጠሪያ ሰፋ ያለ ትርጉም አላቸው፡፡
- ሴክሽዋሊቲ/ Sexuality – ሰዎች እራሳቸው የሚገልጹበት መንገድ ሲሆን ይህም በተፈጥሮ ጾታ፣ በጾታ ማንነት እና አገላለጽ፣ መማረክ እና ተግባር ጽንሰ ሃሳቦች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ባህል እና ሃይማኖት ሰዎች እራሳቸው የሚገልጹበትን መንገድ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አለው፡፡
- የጾታ ማንነት/Gender identity – የአንድ ሰው የማያቋርጥ እና ስሙሙ ወንድ ፣ ሴት ወይም አንድሮጂን የመሆን ውስጣዊ ስሜት ነው ፡፡ ከጨቅላነት ግዜ ጀምሮ በውስጣችን የምናጎለብተው የጾታ (Gender) ሚና እና ግንዛቤ ሲሆን በጉርምስና ወቅት ጎልቶ የሚታይ ወይም የሚወጣ ነው፡፡
- የጾታ ሚና/ Gender role ፡ በማኅበረሰብ የተደነገገ ወይም በልምምድ ጸባይ ላይ የተመሰረተ የስራ ክፍፍል እና ኃላፊነቶችን ለወንድ እና ሴት በመለያየት በቅድመ ሁኔታነት የሚያስቀምጥ ነው፡፡
- ትራንስጀንደር/Transgender – ትራንስ-ሴክሽዋልን፣ትራንስቬስታይትን፣ ክሮስ-ድረሰርስን፣ ድራግ ኩዊን እና ኪንግስ፣ጀንደር ኩዊሮችን እና ሌሎች የመሳሰሉትን የሚያጠቃልል አቃፊ ቃል ነው፡፡
- ትራንስ ማን/ Trans man – የውልደት ጾታው (Sex) ሴት ሆኖ ነገር ግን የጾታ ማንነቱ (Gender identity) ወንድ የሆነ ማለት ነው፡፡ ሁልጊዜ ተባዕታይ ተውላጠ ስም በመጠቀም እንገልፃቸዋለን፡፡
- ትራንስ ዉማን/ MTF/ Trans women – የውልደት ጾታዋ (Sex) ወንድ ሆና ነገር ግን የጾታ ማንነቷ (Gender identity) ሴት የሆነች ማለት ነው፡፡ ሁልጊዜ አንስታይ ተውላጠ ስም በመጠቀም እንገልፃቸዋለን፡፡
- ትራንስ-ሴክሽዋል/ Transsexual – ውጫዊ አካላዊ አገላለጹን ውስጣዊ ከሆነ ጾታዊ ማንነቱ ጋር በህክምና የማስማማት ሂደት ላይ ያለ ወይም የሚሻ ትራንስጀንደር ሰው ነው፡፡ ሁሉም ትራንስጀንደር ሰዎች የመራብያ አካላት ቀዶ-ጥገና ላያደርጉ ይችላሉ፡፡
- ትራንዚሽኒንግ/ Transitioning – አንድ ሰው ውጫዊ አካላዊ አገላለጹን ውስጣዊ ከሆነ የጾታ ማንነቱ (Gender identity) ጋር የማስማማት ሂደት ነው፡፡ ለትራንስጀንደር ሰዎች ይህ ሂደት የመራብያ አካላት ቀዶ-ጥገናን እና ሆርሞን ህክምናን ሊያካትት ይችላል፡፡
- ትራንስቬስታይት/Transvestite – የተቃራኒ ጾታን አልባሳት ለተለያየ ምክንያት የሚለብስ/የምትለብስ ሰው ሲሆን ጾታውን/ዋን ወይም ተክለ ሰውነታቸውን የማስቀየር ፍላጎት ግን የላቸውም፡፡
- ሲስጀንደር/ Cisgender ፡ የጾታ ማንነታቸው (Gender identity) እና የውልደት ጾታቸው (Sex) ተመሳሳይ የሆኑ ሰዎች ማለት ነው፡፡
- ጀንደር ኩዊር/ Gender queer ፡ ለጾታ ማንነት (gender identity) ወንድ እና ሴት ከሚለው የጾታ ሁለትዮሽ አገላለጽ እና ከሄትሮኖርማቲቪቲ ውጪ ለሆኑ ሰዎች አቃፊ ቃል ነው፡፡ ጀንደር ኩዊር ሰዎች እራሳቸው ወንድም ሴትም ሁለት ጾታ (bigender) ፤ወንድም ሴትም ያልሆኑ (agender)፤ በሁለቱ ጾታዎች (gender) ላይ ተመላላሽ ( genderfluid) ወይም ደግሞ ሶስተኛ ጾታ (third gendered) ብለው እራሳቸውን ይገልጻሉ፡፡
- አንድሮጂኒ/ Androgyny – በተለምዶ ግልጽ የሆነ የወንድነት ወይም የሴትነት መለያ አካላዊ ገጽታ እና ባሕርያት የሌለው/ላት
- ኢንተርሴክስ (ፍናፍንት) – ሁለቱንም የጾታ መራቢያ አካላት ይዞ የተወለደ እና በግልጽ የወንድ ይሁን የሴት የመራቢያ አካል መሆኑን መለየት የሚያዳግት፡፡
- ሴክሽዋል አይደንቲቲ/ Sexual identity – አንድ ሰው እራሱን እንደ ወንድ፣ሴት፣ወንድነት(ማስኩሊን)፣ ሴትነት(ፌሚኒን)፣ወይም የነዚህ ጥማሬ እና የራስ ጾታዊ ማንነትን የሚያጠቃልል ነው፡፡
- ሴክሽዋል ኦሪዬንቴሽን/ Sexual orientation – በሁለት ሰዎች መካከል በተለያየ ደረጃ በስሜት፣ በአካል፣ በአስተሳሰብ፣ በመንፈሳዊነት እና በተራክቦ ሥጋ መማረክ ነው፡፡
- ሴክሽዋል ፐራክቲስ/ Sexual practices – በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ ሰዎች፤ በተናጠል ወይም በጋራ የሚደረጉ ወሲባዊ እርካታን የሚያስገኙ ወሲባዊ አድራጎቶች ናቸው፡፡
- ኤምኤስኤም/ MSM – ከተመሳሳይ ጾታ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት የሚያደርግ ወንድ ፡፡ ይህ አገላልጽ የወሲብ ክንውን ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህ ተግባር የጾታ ማንነታቸውን አይወስንም ፡፡
- ደብሊውኤስደብሊው/ WSW -ከተመሳሳይ ጾታ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት የምታደርግ ሴት፡፡ ይህ አገላልጽ የወሲብ ክንውን ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህ ተግባር የጾታ ማንነታቸውን አይወስንም ፡፡
- ሆሞሴክሽዋል/ Homosexual – በሁለት ተመሳሳይ ጾታዎች መካከል በተለያየ ደረጃ በስሜት፣ በአካል፣ በአስተሳሰብ፣ በመንፈሳዊነት እና በተራክቦ ሥጋ መማረክ ሲሆን ለዚህም ወነኛ ሚና የሚጫወተው የተማራኪው ጾታ(Sex) ነው፡፡
- ሄትሮሴክሽዋል (በተለምዶ ቀጥ የምንለው)/ Heterosexual/ Straight – በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች መካከል በተለያየ ደረጃ በስሜት፣ በአካል፣ በአስተሳሰብ፣ በመንፈሳዊነት እና በተራክቦ ሥጋ መማረክ ሲሆን ለዚህም ወነኛ ሚና የሚጫወተው የተማራኪው ጾታ (Sex) ነው፡፡
- ባይሴክሽዋል/ Bisexual – ጾታዊ (Sexual) ዝንባሌ እና ማንነት ሲሆን የዚህ ዓይነት ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች ለተመሳሳይ ወይም ለተቃራኒ ጾታ በስሜት፣ በአካል፣ በአስተሳሰብ፣ በመንፈሳዊነት እና በተራክቦ-ሥጋ ፍላጎት መሳብ ሲሆን ይህ ማለት ግን ለሁለቱም ጾታዎች በአንድ ጊዜ እና በእኩል መጠን ላይሆን ግን ይችላል፡፡
- ጌይ/ Gay – የወንድ ተመሳሳይ ጾታዊ ማንነት (sexual identity) እና ጾታዊ ዝንባሌ (orientation) ፡፡ በተለያየ ደረጃ ሁለት ወንዶች በስሜት፣ በአካል፣ በአስተሳሰብ፣ በመንፈሳዊነት እና በተራክቦ ሥጋ መማረክ፡፡
- ሌዝቢያን/ Lesbian – የሴት ተመሳሳይ ጾታዊ ማንነት (sexual identity) እና ጾታዊ ዝንባሌ (orientation) ፡፡ በተለያየ ደረጃ በሁለት ሴቶች መካከል በስሜት፣ በአካል፣ በአስተሳሰብ፣ በመንፈሳዊነት እና በተራክቦ ሥጋ መማረክ፡፡
- አሴክሽዋል/ Asexual – የወሲብ ፍላጎት የሌለው/ላት
- ሴክሽዋል ፍሉዲቲ/ Sexual fluidity – በራስ ተነሳሽነት የሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነት::
- ሴክሽዋል ማይኖሪቲ/ Sexual minority – ከአብዛኛው ማኅበረሰብ ጾታዊ ማንነት፣ዝንባሌ እና ተግባሮች የተለዩ ጾታዊ ማንነት፣ዝንባሌ እና ተግባሮች ያላቸው ሰዎች፡፡
- ካሚንግ አውት/ Coming out ፡ አንድ ሰው የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ እንዳልሆነ የመረዳት እና እራስን የማግኘት ሂደት ነው፡፡
- የጾታ ጥቃት/ Gender based violence ፡ ጾታን (Gender) መሰረት ያደረገ ጥቃት ሲሆን ሴቶችን ሴት በመሆናቸው፤ ወንዶችን ወንድ በመሆናቸው እና በሚኖሩበት ማኅበረሰብ በሚጠበቅባቸው ግዴታ ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችም የዚህ ጥቃት ሰለባዎች ሲሆኑ የዚህም ምክንያቱ ደግሞ የጾታዊ ማንነታቸው (Gender identity) እና አገላለጽ (Gender presentation) ነው ፡፡
- ሆሞፎብያ/ Homophobia – ለተመሳሳይ ጾታ ፍቅር ስሜቶች፣ እሳቤዎች፣ ባህርያት እና ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ኢምክንያታዊ የሆነ ፍርሃት እና የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ማንነቶችን የማጥላላት ዝንባሌ ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ አግባብ የሌለው ጥላቻ፣ መገለል እና አድልዎን በተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ላይ ያመጣል፡፡
- ኢንተርናላይዝድ ሆሞፎቢያ/ Internalized Homophobia – አንድ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ግለሰብ በማኅበረሰብ ውስጥ የሚደርስበትን ጥላቻ ወደ እራሱ በማስረፅ የራሱን ማንነት እንደ ጉድለት አድርጎ መመልከት፡፡
- ትራንስፎብያ/ Transphobia – ለትራንስጀንደር ሰዎች ኢምክንያታዊ የሆነ ፍርሃት እና የባህርይ ጠባብነት የማሳየት ዝንባሌ ነው፡፡